U.S. Embassy Addis Ababa launches blog

Patricia Haslach

On behalf of the U.S. Embassy in Addis Ababa, I am pleased to announce the launch of our official blog, Kimsha. In one of the local languages, Amharic, Kimsha signifies a “tidbit” or “small taste” of something. Our blog aims to provide timely and relevant information in small bites to members of the public interested in learning more about the work of the U.S. Embassy and American culture.

Each week, blog posts will examine topics involving American values, culture and foreign policy objectives relevant to Ethiopia and Ethiopians. I encourage readers to post comments and questions on the blog and to make it as interactive as possible. We want to hear your views and respond to your comments and questions!
With the launch of Kimsha, U.S. Embassy Addis Ababa looks forward to strengthening our dialogue with Ethiopians and other interested readers and to provide them with interesting news and information.
With that, I hope you enjoy our new offering, Kimsha! Amaseganehlu! –
-Ambassador Patricia M. Haslach, U.S. Ambassador to Ethiopia

አዲስ አበባ የሚገኘውን የአሜሪካ ኤምባሲ በመወከል ቅምሻ የተሰኘ ጦማር መጀመራችንን ስገልጽ በታላቅ ደስታ ነው፡፡ ዓላማችን ጦማሩ ወቅታዊና ጠቃሚ የሆኑ የኤምባሲውን ተግባራት፤ እንዲሁም ከአሜሪካን ባህል ጋር ተያያዥነት ያላቸውን መረጃዎች ለታዳሚው ማህበረሰብ በጥዑም ቅምሻ መልክ እንዲያደርስ ነው፡፡

ጦማሩ በየሳምንቱ ለኢትዮጵያና ለኢትዮጵያውያን ቅርበት ያላቸውን የአሜሪካ እሴቶች፣ባህልና የውጭ ግንኙነት ፖሊሲ ዓላማዎችን ያቀርባል፡፡ መድረኩ ሀሳቦችን የምንለዋወጥበት ይሆን ዘንድ አንባቢያን ያላችሁን አስተያየቶችና ጥያቄዎች እንድታደርሱን እየጋበዝኩ፤ለጥያቄዎቻችሁም ሆነ ለአስተያየቶቻችሁ ወቅታዊ ምላሽ የምንሰጥ መሆኑን ለመጠቆም እወዳለሁ፡፡

ይህን ቅምሻ የተሰኘ ጦማር መጀመራችንን ሳበስር፤ ኤምባሲው ከኢትዮጵያውያንም ሆነ ከሌሎች አንባቢዎቻችን ጋር ተቀራርቦ የሚነጋገርበት መድረክ እንደሚሆንና ለአንባቢዎቻችንም ወቅታዊና ጠቃሚ ዜናዎችንና መረጃዎችን የምናቀርብበት እንደሚሆን እምነቴ ነው፡፡

ቅምሻን እንደምትወዱት ተስፋ አደርጋለሁ! አመሰግናለሁ!

አምባሳደር ፓትሪሺያ ሃስላክ፣ በኢትዮጵያ የአሜሪካ አምባሳደር