Using Intellectual Property to Protect Ethiopia’s Unique Culture

Ethiopia.  Land of Origins.  I saw the phrase in an advertisement for Ethiopia about two months before I was scheduled for my first trip to Addis Ababa.  Now that I have been here, I realize how accurate that phrase is and how critical intellectual property can be in protecting the uniqueness that is Ethiopia.  It has been an honor to come here as part of the U.S. State Department’s public speaker series and share experiences and ideas on how to use intellectual property to protect Ethiopia’s creative and business communities.  I am Professor Emeritus at The John Marshall Law School in Chicago Illinois. I have worked with governments in other African countries on intellectual property protection, including Senegal, Guinea and Botswana.  It was a pleasure to finally make it around the horn to Ethiopia.

DL_AC 1

I had the opportunity to meet with some of Ethiopia’s most creative people – musicians, writers, filmmakers and fashion designers – who are bringing Ethiopia’s unique voices and visions to the world.  According to a recent study by the World Intellectual Property Organization, the copyright industries in Ethiopia represented by these talented artists contributes nearly 5% of the Gross Domestic Product and employs over 4.2% of the urban population.  Yet piracy rates are so high that the Ethiopian Intellectual Property Office (EIPO) reports that over 80% of all music sales in Ethiopia are pirated.  That represents a terrible loss of income to the people whose music makes our lives so much brighter.  Worse, it is income that is stolen by pirates who are nothing but rent seekers, taking money even though they contribute nothing to the process.  Fortunately, I also had a chance to conduct a full-day workshop on enforcement at EIPO where police, prosecutors, customs officials, artists and other stakeholders discussed, not only the critical importance of stronger IP protection, but practical issues in ensuring such protection.

While in Addis Ababa, I also had the chance to meet with a wide array of business people, from small shop owners to the officers in large multinationals who are investing in new businesses in Ethiopia.  There is an energy and excitement in the air that is invigorating.  We discussed the critical need for all business owners to register their marks with the EIPO so that they can protect their goods and services from the scourge of counterfeiting.  If pirates steal the income from local artists, counterfeiters threaten us all with cheaply made goods that fall apart and are not worth the Birr we spent.  Worse, they sell drugs, cosmetics, and auto parts, among other items, that are actually harmful.   I gave a public lecture at the Addis American Center giving some advice on how to avoid buying such goods, and ways we can all work together to remove these items from the marketplace.   I also had a chance to give a lecture at the University of Addis Ababa where we discussed additional ways that Ethiopia can strengthen its current system to provide even greater protection for Ethiopian creators, inventors and businesses.

My fondest memories of Ethiopia will always be the people I met, the amazing cultural heritage that lies at the center of Ethiopia’s uniqueness, and the diversity in flavor of Ethiopian coffees.  I am looking forward to returning and learning more about this amazing Land of Origins in the future!

(Professor Emeritus Doris Estelle Long, The John Marshall Law School, Chicago, USA)

(The views in this piece are those of the author and do not necessarily reflect those of the U.S. government.)

 

 

አእምሮአዊ ንብረት ለባህል ጥበቃ

ኢትዮጵያ፤ ምድረ ቀደምት፡፡ ይህን ሐረግ ለመጀመሪያ ጊዜ ወደ አዲስ አበባ ከመምጣቴ ከሁለት ወር በፊት፤ ኢትዮጵያን ለማስተዋወቅ በተሰራ ማስታወቂያ ላይ ተመልክቸዋለሁ፡፡ እዚሁ ከተገኘሁ በኋላም፤ አገላለጹ ትክክል መሆኑን እና አእምሮአዊ ንብረት፤ ልዩ ለሆነች ኢትዮጵያ ጥበቃ ለማድረግ እጅግ አስፈላጊ መሆኑን ተረድቻለሁ፡፡ በአሜሪካ የውጭ ጉዳይ መሥሪያ ቤት አማካይነት፤ በንግግር አቅራቢነት ተጋብዤ፤ አእምሮአዊ ንብረትን ለኢትዮጵያውያን የፈጠራ ሰዎች እና የንግዱ ኅብረተሰብ ጥበቃ ማዋል በሚቻልበት መንገድ ያለኝን ልምድና ሀሳብ ለማካፈል ወደ ሀገሪቱ በመምጣቴ ክብር ይሰማኛል፡፡ እኔ በኤሊኖይ ቺካጎ በሚገኘው የጆን ማርሻል የህግ ትምህርት ክፍል ፕሮፌሰር ስሆን፤ በአእምሮአዊ ንብረት ጥበቃ ጉዳዮች ሴኔጋል፤ ጊኒ እና ቦትስዋናን ጨምሮ ከሌሎች የአፍሪካ መንግሥታት ጋር ሰርቻለሁ፡፡ አሁን ደግሞ፤ በአፍሪካ ቀንድ ከምትገኘው ኢትዮጵያ በመምጣቴ ደስ ብሎኛል፡፡

በኢትዮጵያ ቆይታዬም፤ የሀገሪቱን ለየት ያሉ ድምጾች እና ራዕዮችን ለዓለም መድረክ ከሚያበቁ እና እጅግ ፈጣሪ ከሆኑ አንዳንድ ሙዚቀኞች፤ ጸሐፊዎች፤ የፊልም እና ፋሽን ባለሙያዎች ጋር የመገናኘት ዕድሉ ነበረኝ፡፡ በዓለም አቀፉ የአእምሮአዊ ንብረት ድርጅት የተሰራ የቅርብ ጊዜ ጥናት እንደሚያመለክተው፤ በእነኚህ የተሰጥዖ ባለቤቶች የሚወከለው የቅጂ መብት ኢንዱስትሪ፤ በሀገሪቱ ጥቅል ዓመታዊ የምርት እና አገልግሎት ዋጋ (GDP) የሚኖረው ድርሻ 5 በመቶ ሲሆን፤ 4.2 በመቶ የሚሆነው የከተማ ነዋሪ በዚህ ዘርፍ ይተዳደራል፡፡ ሆኖም፤ የቅጂ መብት ጥሰት በእጅጉ በመበራከቱ፤ 80 በመቶ የሚሆነው የሙዚቃ ሽያጭ በህገወጥ መንገድ የሚባዛ እንደሆነ የኢትዮጵያ የአእምሮአዊ ንብረት ጽ/ቤት ሪፖርት ያመለክታል፡፡ ይህም በሙዚቃቸው ህይወታችንን ብሩህ ለሚያደርጉ ሰዎች ትልቅ ኪሳራ ነው፡፡ ጉዳዩን የከፋ የሚያደርገው ደግሞ የሌላውን ሰው የአእምሮ ውጤት በመዝረፍ ኪሳቸውን የሚያደልቡት፤ በዘርፉ ሚና የሌላቸው ኪራይ ሰብሳቢዎች መሆናቸው ነው፡፡ እንደ እድል ሆኖ በኢትዮጵያ የአእምሮአዊ ንብረት ጽ/ቤት ተገኝቼ የህግ አፈጻጸምን የተመለከተ የሙሉ ቀን ዎርክሾፕ ለፖሊስ አባላት፤ አቃቢያነ ህጎች፤ የጉምሩክ ሃላፊዎች፤ አርቲስቶች እና ሌሎች ባለድርሻ አካላት በሰጠሁበት ጊዜ፤ ተሳታፊዎች ስለጠንካራ የአእምሮአዊ ንብረት ጥበቃ አስፈላጊነት ብቻ ሳይሆን ስለአተገባበሩም የመወያየት አጋጣሚው ነበራቸው፡፡

በአዲስ አበባ በነበረኝ ቆይታም፤ ከትናንሽ ሱቆች እስከ ትላልቅ ኅብረ-ብሔራዊ ተቋማት ውስጥ የሚሰሩ ሃላፊዎችን ጨምሮ በኢትዮጵያ በአዳዲስ የንግድ ሥራዎች ከሚሰማሩ የተለያዩ አካላት ጋር በነበረኝ ግንኙነት ዘርፉ ጥሩ መነቃቃት እየታየበት መሆኑን ተነግዝቤያለሁ፡፡ ምርቶችና አገልግሎቶች ተመሳስለው ከመሰራት አባዜ እንዲጠበቁ ለማስቻል ሁሉም የንግድ ድርጅት ባለቤቶች የንግድ ምልክቶቻቸውን በኢትዮጵያ የአእምሮአዊ ንብረት ጽ/ቤት የማስመዝገብ አስፈላጊነትን እንዲረዱ የሚያስችል ውይይት አካሂደናል፡፡ ዘራፊዎች፤ አርቲስቶቹ ማግኘት የሚገባቸውን ገቢ የሚነጥቁአቸው ከሆነ፤ አስመስሎ ሰሪዎች በቀላሉ የሚበላሹ እና የከፈልነውን ገንዘብ የማይመጥኑ እጅግ ርካሽ በሆኑ ቁሶች ያጥለቀልቁናል፡፡  አስከፊው ነገር ደግሞ እነኚህ አካላት ጎጂ የሆኑ መድሃኒቶችን፤ መዋቢያ ቁሶችን እና ምትክ የተሸከርካሪ አካላትን ጨምሮ ሌሎች ቁሶችን ለሽያጭ የሚያቀርቡ መሆናቸው ነው፡፡ በአዲስ አበባ በሚገኘው የአሜሪካ ማዕከል ባደረኩት ገለጻ፤ እነኚህን የመሳሰሉ ሸቀጦችን ከመግዛት ስለመቆጠብና ጭራሹኑ ከገበያው በጋራ ስለምናስወግድበት መንገድ ምክር ቢጤ ለግሻለሁ፡፡ እድል ገጥሞኝ በአዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ ባደረኩት ትምህርታዊ ገለጻም፤ ኢትዮጵያ አሁን ያላትን ሥርዓት በማጠናከር፤ በፈጠራ ሥራ እና በንግዱ ዘርፍ ለተሰማሩ ዜጎቿ ጠንከር ያለ ጥበቃ ማድረግ ስለምትችልበት ሁኔታም ሀሳብ ተለዋውጠናል፡፡

ያገኘኋቸው ሰዎች፤ ኢትዮጵያን ልዩ የሚያደርጓት ሳቢ የሆኑ ባህላዊ ቅርሶቿ እና ባለብዙ ጣዕም ቡናዋ ጣፋጭ ትዝታን ጥለውብኛል፡፡ ወደፊት፤ ስለዚህች ማራኪ ምድረ ቀደምት ሀገር ተመልሼ ብዙ የመማር እቅድ አለኝ፡፡

(ፕሮፌሰር ዶሪስ ኤስተለ ሎንግ፤ በአሜሪካ ቺካጎ በሚገኘው የጆን ማርሻል የህግ ትምህርት ክፍል የሚያገለግሉ የካበተ ልምድ ያላቸው ምሁር ናቸው)

(ከላይ በሰፈረው ጽሑፍ የተካተተው ሀሳብ የጸሐፊውን የግል አስተያየት እንጂ የአሜሪካን መንግሥት አቋም አያንጸባርቅም)

 

 

 

 

 

 

 

 

 

 

 

 

 

Leave a comment